ጥናት 2 ጥያቄዎች

ውግዘት (1:6-10)

6

በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤

7

እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ።

8

ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።

9

አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።

10

ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም።

 

                                           ጥያቄዎች

  •          ጳውሎስ እደነቃለው ማለቱ ምን ማለት ነው?
  •        ልዩ ወንጌል ምን አይነት ነው?
  •         የተረገመ ይሁን ማለት ምን ለማለት ነው?
  •       የክርስቶስ ባሪያ ምን አይነት ባህሪ አለው?

 






Comments

  1. 1.እደነቃለሁ=የስገርመኛል በዝህ አጭር ጊዜ ውስጥ ከመጀመሪያው የወንጌል መልዕክት መንሸራተተቹ::
    2.መዳን በእየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት በማመን የምገኝ ፅድቅ መሆኑን እየታወቀ :ከዝህ የተለየ ወንጌል ማለት ነው::
    3.የተረገመ-የተወገዘ :የተተዐ ይሁን
    4.ለመንፈስ ቅዱስ አሰራር የተመቻቸ በእግዝሀብሄር ፍቃድ የምመላለስ

    ReplyDelete

Post a Comment

የአንባቢዎች ብዛት

Popular posts from this blog

የገላትያ መጽሐፍ ጥናት 1

ጥናት 2 መልሶች