ጥናት 2 መልሶች
የጥናት ሁለት መልሶች ከማብራሪያ ጋር ጳውሎስ እደነቃለው ሲል የተታለሉትን ገላትያውያን አማኞችን በዝግታ ሊመክር መጀመሩን አመላካች ነው። እደነቃለው ማለቱ ለእነርሱ ያለውን መልካም መገረም ለመግለጽ አይደለም። የጥሩ ክዋኔ ማበረታቻ ሳይሆን እንደውም እንዳፈረባቸው እና በተፈጠረው ሁኔታ ማዘኑን መቆጨቱን አመላካች ነው። የጳውሎስ ዓላማ ለገላትያ አማኞች ፡ ወደ እውነተኛው የዳኑበት መንገድ እንዲመለሱ በመሆኑ በዝግታና በፍቅር ይናገራቸው ይጀምራል። ምክንያቱም ፡ በጳውሎስ እሳቤ ማንም ቢሳሳት ወደ መልካሙ መንገድ የሚቀናው ወይም የሚስተካከለው በፍቅር እንደሆነ ያምናል ያስተምራልም። ሰዎችን ለመመለስ እየፈረዱ፤ እየጮሁ ፤እያጋጩ የመሄድን ዝንባሌ የጳውሎስ ንጹህ ወንጌል በትምህርቱ አይደግፍም። ለተታለሉ ወገኖች ጥፋታቸውን ሳይሆን መመለሳቸውን መዳናቸውን ስለሚፈልግ በመልካም ንግግር በለዘበ አንደበት ንግግሩን “እደነቃለው “ በሚል የቁጭት እና የመሪር ሃዘን ቃል ይናገራቸዋል። እነዚህን የገላትያ አማኞች ነድፈው የበከሉዋቸው ተንኮለኞች መኖራቸውን መዘንጋት ውስጥ አልገባም ጳውሎስ በመልክቱ ። ነገር ግን ጳውሎስ በወንጌሉ ስብከት ያመኑትን ወገኖች እንደ ወላጅ በ እንክብካቤ መገሰጽን መርጧል። ዋናው ትኩረቱ እነሱን ማትረፍ በመሆኑ ነው። ጳውሎስ በፈተና ተሰናክለው ለወደቁ የሚራራ ቀና መንፈስን ተቀብሏል። ስለ መንጋው እጅግ የሚገደው እረኛ ነበር። ቦታውንና ስሙን ለማስጠበቅ ሳይሆን ነፍሳትን ለማዳን ነበር ግቡ። ነፍሳትን ለማዳን ነበር በብዙ ሺ የሚቆጠር ኪሎሜትሮችን በብዙ ስቃይ እና መከራ ተጉዞ ወንጌሉን በሚሲዮነነት ሲያዳርስ የነበረው። ለህይወቱ ሳይሳሳ የኖረለት ወንጌ...