የጳውሎስ ሐዋርያነት (1:11-12) ማብራሪያ
ጥናት 3 ማብራሪያ
የጳውሎስ ሐዋርያነት (1:11-12)
ወንድሞች ሆይ፥ በእኔ የተሰበከ
ወንጌል እንደ ሰው እንዳይደለ አስታውቃችኋለሁ፤ |
ኢየሱስ ክርስቶስ ገልጦልኛል
እንጂ እኔ ከሰው አልተቀበልሁትም አልተማርሁትምም። |
ይህ ጳውሎስ በተቃዋሚዎቹ ለቀረበበት ክስ ምላሽ የሰጠበት ወሳኝ ሃሳብ ነው። ወንጌሉን ከሰው እንዳልተቀበለው
ይልቅስ ከ እየሱስ ክርስቶስ ከራሱ በመገለጥ እንደተቀበለ እያስረዳ ነው። ወንጌሉ ሰዎች ያቀበሉት አልነበረም። ሰዎችም አላስተምሩኝም
እያለ ነው።
ከሰው አይደለም ሲል ጳውሎስ “ምድራዊ
ወንጌል አይደለም ያለኝ” እያለ ብቻ አይደለም ። ምክንያቱም ተቃዋሚዎቹም
የ እኛ ወንጌል ሰማያዊ ነው ምድራዊ አይደለም ስለሚሉ ነው።
ጳውሎስ እያለ ያለው በሰው እጅ
ተጽፎ ፤ ከሰው እግር ስር ተቀምጬ ወይም በሰው እርዳታ ተነቦልኝ
ያገኘውት ወንጌል አይደለም እያለ ነው። ስለዚህ ከሰው አይደለም ሲል ሰው ድርሻውን አዋጥቶበት በሰው በኩልም እንደ ሰው የተሰጠኝ
ወንጌል አይደለም እያለ ነው።
ኢየሱስ ገልጦልኛል ሲል ወንጌሉን
በልዩ መገለጥ ከ እየሱስ ክርስቶስ ከራሱ እንዳገኘው እየተናገረ ነው።
ጳውሎስ ወንጌሉን ወደ ደማስቆ እየተጓዘ ሳለ እየሱስ ሲገለጥለት ነበር የተቀበለው።
ቅዱስ ሉቃስ በሓዋርያት ምዕራፍ
9 ላይ እየሱስ ከርስቶስ ጳውሎስን ተነስ እንዳለው ወደ ከተማ እንዲገባ
እንደነገረው እና ማድረግ ያለበትን ነገሮች እንደሚነገሩት ነግሮት ነበር።
እየሱስ ክርስቶስ ጳውሎስን ወደ
አናንያ ወንጌሉን እንዲማር አልነበረም የላከው። አናንያ ያደርገው ነገር ጳውሎስን ማጥመቅ እጁን እንደጫነበት ወደ ቤተ ክርስትያንም
እንዲሆን እንደነገረው እናያለን። እርሱ አናንያ ጳውሎስን ያለው ነገር
“ ወንድማችን ጳውሎስ እየሱስን ላንተ እንደተገለጸልህ ለ እኔም ተገልጾ አይንህ እንደሚከፈትና በመንፈስ ቅዱስ እንደምትሞላ ነግሮኛል።
ጳውሎስ ከ አናንያ መመሪያን አልተቀበለም! ጳውሎስ በክርስቶስ እየሱስ ተጠርቶ ፤ ተመርቶ እና ታስቦ የነበረው ገና በደማስቆ በመንገድ ሳለ ነበር። ከ አናንያ ጋር መገንኘቱ ለወንጌሉ መጠራቱ እና መለየቱን
ምስክርነት እንዲሆነው ነበር።
ጳውሎስ ሓሰኞቹን ሓዋርያት በደብዳቤው እንዲገስጽ ያስገደደው ዋና ጉዳይ ፡ - በ እነርሱ የማታለል ስብከት የ እርሱ አገልግሎትና ሃዋርያነት ከሌሎቹ
ያነሰ መሆኑን በሚያታልለው አንደበታቸው እየተናገሩ በመሆኑ ነው።
በዚህች የገላትያ ክልል ቤተ እምነቶች ወንጌሉን በፍጥነት መቀበላቸው እጅግ
የሚያስደስት ነገር ቢሆንም ፤ በ አንድ የሃሰት ዘር ግን ታምሰው በፍጥነት ከ እውነተኛው መንገድ መውጣታቸው እጅግ አሳዛኝ ነበር።
ይህም ትንሽ እርሾ ምን ያህል ሊጥ እንድሚያቦካ እንዲሁ ትንሽ ሃሰት ዘር እርሻውን ሊያምስ ብሎም ወደ ጥፋት ሊያመራ እንዲያደርገው
እንደሚችል ለ እኛም ዘመን አመላካች ነው።
የጽድቅ ትምህርት ተሰባሪ ነው።
የጽድቅ ሃሳብ በራሱ አይደለም ድካሙ ይልቅስ የምናደክመው እኛ ውስጥ
ሲሆን ነው።
በፍጥነት አንድ ሰው ከሚደሰትበት
ወንጌል ሊያፈነግጥ እንደሚችል ማወቅ አለብን። እስከየት ድረስ በ
እምነታችን ልንጸና እንደምንችልም በውስጣችን ይታወቀናል ። ምን ምን ሁኔታዎች ከ እውነት መንገድ እንደሚያዳልጡንም እናውቃለን። በሚያዳልጠው ጎዳና ወንጌሉን ላለመጣል ራሳችንን
እያጽናናን ሳለን ፤ ወዲያው ህግ እያጓራ ህሊናችንን ሊያቃውሰው ይከብበው ይጀምራል ለዛም ወንጌል ተሰባሪ ነው ነው የምለው ምክንያቱም እኛ ተሰባሪዎች በመሆናችን
ውስጣችን ያለውን እውነት እንደምናቆየው መጠን የሚወሰን በመሆኑ ነው።
እጅግ አስቸጋሪ ጉዞ እንድጓዝ የሚያድርገን ግማሹ እኛነታችን ነው። የእራሳችን ምክንያታዊነት እራሱ ነው ከ እኛ በተቃራኒ የሚቆመው። ስጋችን
መንፈሳችንን ይቃወማል ! ለዛም ነው ክርስቶስን ማወቅ እና ማመን በሰው ጥረት አይገኝም ብለን የምናስተምረው።
እግዚአብሄር ብቻውን በውስጣችን እምነትን መፍጠር ማቆየትም ይችልበታል። እግዚአብሄር
እምነትን በቃሉ መሰረት በውስጣችን ይፈጥራል። በውስጣንም ባለው ቃሉ
እምነታችንን ይጨምራል፤ ያሳድጋል ፤ ያጠነክራል ፤ያረጋግጣል። ስለዚህ ማንም ለ እግዚአብሄር የሚሰጠው ትልቁ አገልግሎት ቃሉን ማድመጡ
ነው።
በሌላ መልኩ የ እግዚአብሄርን ቃል
እንደመተው እጅግ አደገኛ ነገር የለም። በበቂ ሁኔታ ቃሉን አውቃለው በሚል መታለል ቀስ በቀስ የ እግዚአብሄር ቃል ወደ መናቅ ያሸጋግራል
ከዛም ክርቶስንና ወንጌሉን ሙሉ በሙሉ እስከማጣት የሚደርስ ፍጻሜን ያመጣል።
ይህንን ማሰብ መቻል አለብን አማኞች
ወንጌሉን በጥንቃቄ መማር አለባቸው ። በትህትና ጸሎትንም መታገዝ ይኖርባቸዋል። የምንጎድፈው በደካሞቹ ጠላቶቻችን አይደለም እንደውም
እጅግ ጠንካራ በሆኑ እና ሁሌም እየታገሉን ባሉ ጠላቶች ነው።
ጠላቶቻችን እነዚህ ናቸው፡ የገዛ ስጋችን ፤ ይህ ዓለም ፤ህግ ፤ ኃጥያት ፤ሞት ፤ ቁጣና ፍርድ ፤ እና
ዲያብሎስ እርሱ ናቸው።
ዛሬም ሓሰተኛ ሃዋርያ ነን ባዮች
መምህራን የሚያቀርቡት መከራከሪያ ነጥብ አንተ ማንህ የተከበረውን አስተምሮ ውጪ እንዲህ ያለ ትምህርት የምታስተምረው በማለት በማጣጣል
ነው። አንተ ራስህን ከሁሉ ጻድቅ እና ቅዱስ አድርገህ ለምን ታያለህ ? አንተ ክሁሉ በላይ አዋቂ ነህ? እያሉ ሊሎች ህዝቦች ፊት
ተቀባይነት ለማግኘት በመጣር ነው።
ሰይጣንም በምክንያታዊነታችን ታግዞ
በውስጣችን ያለውን ክርክር ያባብሰውና ጫና ይፈጥርብናል። ልባችንን
ግን ጠብቀን እነ ቅዱስ አውግስጢኖስ ፤ ቅዱስ ጳውሎስ ፤ ቅዱስ ዮሐንስ ወይም ከሰማይ የወረደ መላአክ ሰብከው ይሆናል ፤ እኔ ግን
እውነቱን ከመናገር ወደ ኋላ አልልም ስንል ልባችንን አናጣውም ።
ጳውሎስ የሚያስተምረን ሁሌም አገልግሎታችን
እግዚአብሄርን እንጂ ሰውን የሚያከበር ሰው እንዲወደው የሚጥር መሆን እንደሌለበት ነው ። ክብር የ እግዚአብሄር ብቻ በመሆኑ።
ወንጌል እውነት የሚሆነው የሰውን
ክብር ነጥቆ ሙሉ ክብርን ለፈጠረው አምላኩ ሲሰጥ ነው።
ለ እግዚአብሄር ብዙ ክብር መስጠት
ምንም የጎንዮሽ ጉዳት የለውም።
በጊዜው ጲጥሮስ ተሳስቶ ነበር።
ጳውሎስ የጴጥሮስን ስሀተት አርሟል እንጂ ቅዱስ ሆይ አንተ መንፈስ ቅዱስ አለብህ አትስተካከልም አላለውም ። ምክንያቱም የጴትሮስ
በ አይሁዳዊነቱ የመሳብ ስህተት ሙሉ ቤተክርስቲያኒቱን ይጎዳ ስለነበር ነው። ደግሞም የ ከእግዚአብሄር የሆነ አልነበረም።
ዛሬም በበተክርስቲያን ጳውሎስ፤
ጰጥሮስ ፤ ሓዋርያ እከሌ ፓስተር እከሌ ቄስ እከሌ የእግዚአብሄርን ወንጌል እስካላስተማሩ ድረስ ስለተከበሩ በሚል ሞኝነት እንዲሁ መስማት የለብንም ። ለዛም ነው ማንም አስተማሪ ለሚያስተምረው ትምህርት
በከርስቶስ መጠራቱን ማረጋገጥ አለበት እያለ ያለው ሃዋርያው ጳውሎስ።
ጳውሎስ አገልግሎቱን ከ እየሱስ
ክርስቶስ ከራሱ ስለተቀበል እውነተኛ መሆኑን ያስረዳል። እጅግ ውጤታማ የወንጌል ስብከትም ያደረገበት ዋና ምክንያት ይህ ነበር።
Comments
Post a Comment