ትውውቅ መግቢያ (1:1-5) ጥያቄዎች

ትውውቅ መግቢያ (1:1-5)

ወደ ገላትያ ሰዎች 1

1-2

በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ያልሆነ ጳውሎስ ከእኔም ጋር ያሉት ወንድሞች ሁሉ፥ ወደ ገላትያ አብያተ ክርስቲያናት፤


3

ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።


4

ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ ስለ ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ።


5

ለአብ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።


 

ጥያቄዎች

1.       ጸሃፊው ስለ ራሱ ምን ይላል? ሃዋርያነቱን እንዴት ይታያል?

2.      ገላትያ አብያተክርስቲያናት ሲል ምን ማለቱ ነው?

3.      ይህንን ዓለም ከ ደህንነት ፤ ከአብ እና ወልድ እንዲሁም ከ ሃጥያት ጋር ያላቸውን ግንኙነት አብራሪ

ተዛምዶ

1.       ከዚህ ጥናት ምን እንማራለን ?

Comments

የአንባቢዎች ብዛት

Popular posts from this blog

የገላትያ መጽሐፍ ጥናት 1

ጥናት 2 ጥያቄዎች

ጥናት 2 መልሶች