ታሪካዊ ዳራ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን፣ በቤተክርስቲያን አብዛኞቹ ቀደምት ክርስቲያኖች አይሁዳውያን የነበሩ ሲሆን በሃይማኖት ወጎችና በጁዳይዝም ህግጋት ሞግዚትነት ስር እያደጉ ያሉ ሰዎች ነበሩ፡፡ ሆኖም እነዚህ አይሁዶች ክርስቶስን መከተል ሲጀምሩ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የነበሯቸው ግንኙነቶች ተለወጡ፡፡ ከዚያም በክርስቶስ አማካይነት የእግዚአብሔርን ሙሉ መገለጥ ስላገኙ ወደ መንፈሳዊ በሳልነት የሕይወት እርከን አደጉ፡፡ ሆኖም ጥቂት ቆይተው፣ እነዚህ ቀደምት አይሁዳውያን ክርስቲያኖች የለመዱትን የአሮጌውን የአይሁድ ልምምዳቸውን ሲያጡ ምቾት አልሰማ ይላቸው ጀመር፣ ስለዚህ የክርስትና እምነታቸውን አሁን እየተዉት ካለው አይሁዳዊ ልማዳቸው ጋር መቀየጥ ጀመሩ ሌሎችም ያንኑ እንዲያደርጉ ያስገድዱ ጀመር፡፡ 1. አይሁዶች ለ ክርስትና ቀደምት (ጀማሪዎች ) ናቸው 2. አይሁዶች በይሁዲ ትምህርትና ስራዓት ያደጉ ናቸው 3. በአዲሱ እና በቀደመው ህይወት መካከል የተፈጠረ ጥል 4. በልማድ የተቀየጠ ወንጌል መፈጠሩ ጸሃፊው፡ ሀዋርያው ጳውሎስ ሚሲዮን ነበር። ፡ ሚሲዮን ከመኖሪያ ሃግሩ ውጪ የተላከ መልክተኛ ነው። ፡ ሚስዮን ልዑክ ማለት ነው። የገላትያ አብያተክርስቲያናት የነበሩበት ሁኔታ ምን ነበር የአህዛብ መብዛት ሀሰተኛ መምህራን መበራከታቸው
Comments
Post a Comment