ጥናት 3 ማብራሪያ ይህ ጳውሎስ በተቃዋሚዎቹ ለቀረበበት ክስ ምላሽ የሰጠበት ወሳኝ ሃሳብ ነው። ወንጌሉን ከሰው እንዳልተቀበለው ይልቅስ ከ እየሱስ ክርስቶስ ከራሱ በመገለጥ እንደተቀበለ እያስረዳ ነው። ወንጌሉ ሰዎች ያቀበሉት አልነበረም። ሰዎችም አላስተምሩኝም እያለ ነው። ከሰው አይደለም ሲል ጳውሎስ “ምድራዊ ወንጌል አይደለም ያለኝ” እያለ ብቻ አይደለም ። ምክንያቱም ተቃዋሚዎቹም የ እኛ ወንጌል ሰማያዊ ነው ምድራዊ አይደለም ስለሚሉ ነው። ጳውሎስ እያለ ያለው በሰው እጅ ተጽፎ ፤ ከሰው እግር ስር ተቀምጬ ወይም በሰው እርዳታ ተነቦልኝ ያገኘውት ወንጌል አይደለም እያለ ነው። ስለዚህ ከሰው አይደለም ሲል ሰው ድርሻውን አዋጥቶበት በሰው በኩልም እንደ ሰው የተሰጠኝ ወንጌል አይደለም እያለ ነው። ኢየሱስ ገልጦልኛል ሲል ወንጌሉን በልዩ መገለጥ ከ እየሱስ ክርስቶስ ከራሱ እንዳገኘው እየተናገረ ነው። ጳውሎስ ወንጌሉን ወደ ደማስቆ እየተጓዘ ሳለ እየሱስ ሲገለጥለት ነበር የተቀበለው። ቅዱስ ሉቃስ በሓዋርያት ምዕራፍ 9 ላይ እየሱስ ከርስቶስ ጳውሎስን ተነስ እንዳለው ወደ ከተማ እንዲገባ እንደነገረው እና ማድረግ ያለበትን ነገሮች እንደሚነገሩት ነግሮት ነበር። እየሱስ ክርስቶስ ጳውሎስን ወደ አናንያ ወንጌሉን እንዲማር አልነበረም የላከው። አናንያ ያደርገው ነገር ጳውሎስን ማጥመቅ እጁን እንደጫነበት ወደ ቤተ ክርስትያንም እንዲሆን እንደነገረው እናያለን። እርሱ አናንያ ጳውሎስን ያለው ነገር “ ወንድማችን ጳውሎስ እየሱስን ላንተ እንደተገለጸልህ ለ እኔም ተገልጾ አይንህ እንደሚከፈትና በመንፈስ ቅዱስ እንደምትሞላ ነግሮኛል። ጳውሎስ ከ አናንያ መመሪያን አልተቀበለም! ጳውሎስ በክርስ...